ስለ ጽ/ቤቱ

የኮልፌ ቀራኒዮ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት

የኮልፌ ቀራኒዮ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የስራ እድል ፈጠራ፣ የክህሎት ልማት እና የስራ ባለሙያዎችን ብቃት ለማሳደግ የሚሰራ ተቋም ነው።

ጽ/ቤቱ ለአካባቢው ህብረተሰብ የስራ እድል ፈጠራ፣ የስልጠና አገልግሎት፣ የስራ ምዝገባ እና የቅሬታ አፈታት አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ራዕይ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2022 ዓ.ም ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት ምቹ የስራ ሁኔታ የተረጋገጠበት ዘላቂ የስራ እድል ተፈጥሮ ማየት፡፡

ተልዕኮ

ክህሎት መር የውጤት ተኮር የስልጠና ስርዓት በመዘርጋት ብቁ ተወዳዳሪና ሥራ ፈጣሪ የሰው ኃይል በማፍራት፣ ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ በማድረግ ማልማት እንዲሁም ውጤታማ የሆነ የሥራ ስምሪት አገልግሎት በመስጠት ዘላቂ የስራ እድል እንዲፈጠር ማድረግ።

እሴቶች

  • የስራ ባሕል ማዳበር
  • ሙያዊ ልህቀት
  • ጥራትና ተደራሽነት
  • አዳዲስ ፈጠራ ማመንጨት
  • ለለውጥ ዝግጁ መሆን
  • አካታችነት
  • አገልጋይነት
  • ታማኝነት